ሃርቬ ዱራንቶን

ማናጂንግ ዳይረክተር

አዋሽ ወይንን ከመቀላቀሉ በፊት፣ ሚ/ር ሃርቬ ዱራንቶን ከተዋጣለት የስራ ልምድ ጋር በዋና ስራ እስኪያጅነት በፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና አረብኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሃገሮች ውስጥ አገልግሏል፡፡ በነዚህ ቦታዎች የቡድን ስራ አመራር፣ ተሰጥዖ፣ የአንተርፕረነርና የስራ አመራር ክህሎቶችን አበልፅጓል፡፡ ሚ/ር ሃርቬ ከተለያዩ ድርጅቶች የሚከተሉትን የሥራ ልምዶች አካብቷል፡፡ቤልጂየም ውስጥ ባለው ግሩፕ ዩኒብራ በተባለ መስሪያ ቤት ውስጥ በጠመቃ ክፍል፤ ኢኳቶሪያል አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ሞሮኮ፣ ጊኒና ግብፅ ውስጥ ባሉ የኔስል ኩባንያዎች በዋና ስራ አስኪያጅነት፡፡ሃርቬ በሥራ አመራር ከኢኮል ሱፒሪየር ደ ኮሜርስ ቸልርሞንት የማስተሬት ድግሪውን አግኝቷል፡፡

ዴቪድ ስፔለር

ዋና የሂሳብ ሹም

ዴቪድ (ዳዊት) በሂሳብ አያያዝ (አካውንቲንግ) ድግሪውን ይዟል፡፡ በንግድ ጥናቶች ደረጃ-ሀ ላይ ደርሷል፡፡ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን ከመቀላቀሉ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ለአፋር አላን ፖታሽ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል የአክሲዮን ኩባንያ በሂሳብ ዳይረክተርነት ለአራት ዓመታት ሰርቷል፡፡ ዴቪድ በገልፍ ጎልድ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ በሪጅን የሂሳብ ተቆጣጣሪ የሥራ መደብ ለአምስት ዓመታት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡

አለን ማሲነስ

የገበያ ዳይረክተር     

አለን ማሲነስ ስራ የጀመረው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚገኘው ሳብ ሚለር እየተባለ በሚጠራው ድርጅት ውስጥ ነው፡፡ አለን በዚህ ድርጅት ውስጥ ለአስራ-ሁለት ዓመታት ያህል ክህሎቱንና ዕውቀቱን ገንብቷል፡፡ ከዚያም በኋላ፣ እንደ ኬንያ፣ ዛምቢያ፣ ሌሶቶና ቦፅዋና በመሳሰሉት በርካታ ሃገራት በሚገኘው የኮካኮላ ኩባንያ ውስጥ ለስድስት ዓመታት ግልጋሎት አበርክቷል፡፡ በመቀጠልም አለን በጋና፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬት፣ ማላዊና ታንዛኒያ በሚገኘው ካሪስበርግኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ሰርቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አለን የንግድ ዳይረክተራችን በመሆን አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን እያገለገለ ይገኛል፡፡

ሴባስቲየን አኡበርት

የቴክኒክ ዳይረክተር    

ሴባስቲየን በባዮሜዲካል ምህንድስና ሁለተኛ ድግሪውን ከኤትዝዊች፣ የመጀመሪያ ድግሪውን ደሞ በመካኒካል ምህንድስና ከላውሳን የትምህርት ተቋም አግኝቷል፡፡ ለአምስት ዓመታት ያህል ፎናክ ኤ.ጂ. ለተባለ ድርጅት ግልጋሎት ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም በኔስል ስዊትዘርላንድ ለአራት ዓመታት ተቀጥሮ አገልግሏል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሴባስቲየን በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያንየቴክኒክ ዳይሬክተራችን ነው፡፡

ግርማ በለው

የሰው ሃይልና ኦፐሬሽን ዳይረክተር (?)

ግርማ በኢንፎርሜሽን ሲስተም ሁለተኛ ድግሪ፣ በንግድ ስራ አመራር ደሞ የመጀመሪያ ድግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በፕሮጀክት ስራ አመራር የምስክር ወረቀት ተቀብሏል፡፡ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን ከመቀላቀሉ በፊት ግርማ ለአሜሪካው ፕላንድ ፓሬንትሁድ ፌዴሬሽን በቡድን መሪነት ለአንድ ዓመት አገልግሏል፡፡ በተጨማሪም ግርማ በለው እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በኦፐሬሽን ዳይረክተርነት ለአንድ ዓመት ኢትዮ ጆብስን አገልግሏል፡፡

ጆሃን ረዲሊንሄስ

ፋርም ማኔጀር

ጆሃን ረዲሊንሄስ ከስቴሌንቦሽ ዩኒቨርስቲ በግብርና ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን አጠና፡፡ ጆሃን የመጀመሪያ ስራውን በቶርን የወይን ማምረቻ ውስጥ በማድረግ ለ12 አመታት ያክል አገልግሉአል፡፡ ከዚህም በኋላ በአራቤላ የወይን ማምረቻ ወደ 17 ዓመት እርሻ ውስጥ ያገለግል ነበር፡፡ ጆሃን በ 2014 አዋሽ ወይንን በመቀላቀል እስካሁን ድረስ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ሄኖክ በላይ

የልደታ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ

ሄኖክ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪውን በአፕላይድ ኬሚስትሪ፣ አዲስ አበባ በሚገኘው ግሪን ዊች ኮሌጅ ደሞ በዓለም-አቀፍ የንግድ ጥናት ሁለተኛ ድግሪውን አግኝቷል፡፡ በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ከመቀጠሩ በፊት፣ አሰላ በሚገኘው የብቅል ፋብሪካ ውስጥ በኬሚስትነት ለአንድ ዓመት አገልግሏል፡፡ በተጨማሪም አዲስ አበባ በሚገኘው አይ ዞን እየተባለ በሚጠራው ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ውስጥ ለአንድ ዓመት በገበያ ልማት ሰራተኝነት አገልግሏል፡፡

እዮብ አሳምነው

የመካኒሳ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ

እዮብ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ኮሚስትሪ የመጀመሪያ ድግሪ፣ ሁለተኛ ድግሪውን ደሞ በአካባቢ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወስዷል፡፡ እዮብ ሥራ የጀመረው በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያበኬሚስትነት ሲሆን ከዘጠኝ ዓመታት ግልጋሎት በኋላ የመካኒሳ ፍብሪካ ስራ አስኪያጃችን ሆኗል፡፡

ዳኜ በላይ

የግብርና አማካሪ

ዳኜ በእፅዋት ሳይንስ የትምህርት መስክ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ድግሪውን አግኝቷል፡፡ ሥራ የጀመረው በኢትዮጵያ የግብርና ኢንስቲቲዩት ሲሆን፣ በዚሁ መስሪያ ቤት በከፍተኛ የቴክኒክ ረዳትነት ሰፋ ያለ የስራ ልምድ አካብቷል፡፡ ዳኜ ለግብርናው ኢንዱስትሪ የዘዎትር የጋለ ፍቅር ስላለው፣ በዚሁ መስክ ሥራውን ቀጥሏል፡፡ እንዲሁም በግብርና የስራ አስኪያጅ መደብ የአሰላን ሞዴል የግብርና ድርጅት አገልግሏል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ከአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ቤተሰብ ጋራ ተቀላቀለ፡፡ በዚህ ዓይነት ዳኜ ከእኛ ጋር ለስድስት ዓመታት ሰርቷል፡፡

ፀሐዬ ዘረሰናይ

የጥራት ስራ አስኪያጅ

ፀሐዬ በያዘው የስራ መስክ የካበተ ልምድ ይዞ ነው የመጣው፡፡ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን ከመቀላቀሉ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ የመድሃኒት አምራች አክሲዮን ኩባንያ (ኢፋርም) ውስጥ በከፍተኛ የኢንስትሩሜንታል ተንታኝነት፣ በከፍተኛ የኬሚስት ተመራማሪነትና የጥራት ቁጥጥር ሃላፊነት አገልግሏል፡፡ የትምህርት የምስክር ወረቀቶቹ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመድሀኒት ትንተናና የጥራት ማረጋገጫ የመጀመሪያ ድግሪና በፋርማሲ የትምህርት መስክ ደሞ ዲፕሎማን ያካትታሉ፡፡

ሐይማኖት ወ/ፃዲቅ   

ኢ.ኤች.ኤስ. አማካሪ

ሐይማኖት ትምህርቷን የተከታተለችው በሩሲያ ሲሆን፣ ከቮልጎ ግራድ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ስነ-ህይወት (ባይዎሎጂ)፣ ኬሚስትሪና ግብርና አጥንታለች፡፡ ሁለተኛ ድግሪዋን ከያዘች በኋላ በጥራት አስተዳደር የትምህርት መስክ አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው ሮችቪል ኦን ላይን (የመፃፃፍ) ዩኒቨርሲቲ ፒ.ኤች. ድግሪዋን በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ ሐይማኖት በኢትዮጵያ የሕዝብ ጤና ኢኒስቲቲዩት ውስጥ በፓስተርነት ነው ስራዋን የጀመረችው፡፡ በመቀጠልም የራሷን ንግድ ለመጀመር በመወሰን ጎልደን ብሪጅ የምክር አገልግሎት የሚል ድርጅት ከፈተች፡፡ በ1975 አ.ኤ.አ. አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን በመቀላቀል እስካሁን ከእኛ ጋር እየሰራች ትገኛለች፡፡

 ኦሬሊ ሞተት

የግዢና ሰፕላይ ቼይን ስራ አስኪያጅ

ኦሬሊ ሞተት ከስዊዙ ሉዛን ፌዴራል የቴክኖሎጂ ተቋም በማቴሪያል ሳይንስ እና ምህንድስና ሁለተኛ ዲግሪዋን ይዛለች፡፡ አዋሽ ወይንን ከመቀላቀሏ ቀደም ብሎ በስዊዘርላንድ ኤቢቢ ሴሚኮንዳክተር፣ ስዊዝ ስታርታፕ ቴክኖሎጂ እና በአልትራን ኤጂ ኩባንያዎች በ ሰፕላይ ቼይን የሥራ መደብ ለበርካታ አመታት ሰርታለች፡፡

 

 

ሪቻርድ ኦተር

ቪቴ ካልቸር ማስተር

ሪቻርድ ኦተር አዋሽን የተቀላቀለው በቪቴ ካልቸር ማስተር ሲሆን  በቪቴ ካልቸር አኖሎጅ፣ በቢዝነስ እና ትሬድ የስራ መደቦች በአማካሪነት እንዲሁም በቴክኒክ ማናጀር፤ በአስተማሪነት፤ በወይን ሜከር እና በቬንያርድ ከርየሽን በተለያዩ ድርጅቶች የ27 አመታት የስራ ልምድ ያካበተ ነው፡፡