ከተከሽኖ የማስተዋወቅ ዘመቻ ጋር ተያይዞ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ የምርት አቅራቢ ደንበኞቹን የስራ ውጤት ጥልቅ በሆነ ስሜት ያደንቃል፡፡ ስለዚህም ነው የምርት አቅራቢዎቹ የመጠጥ ተጠቃሚ ድንበኞቻቸውን ከራሳቸው ጋር አቆይተው ይይዙ ዘንድ አስፈላጊውን የክህሎት ስልጠና እየሰጠን የምንገኘው፡፡ የአፕሬቲቭ መጠጦችን የመጠቀሙ ባህል በኢትዮጵያችን እያደገ መጥቷል፡፡ የሄንን ለማበልፀግና የአዋሽ ምርቶች በተመሳሳይ ሁኔታ የሚካተቱበትን ዕድል በማመቻቸትም ረገድ እያደረግን ባለው አስተዋጽኦ እጅግ ደስተኞች ነን፡፡ የተከሽኖ ዘመቻችን ዋና ትኩረቱ ደንበኞቻችን ዛሬና ወደፊት የሚደሰቱባቸውን አዳዲስና አስደሳች የድብልቅ መጠጥ ዓይነቶችን እንዲፈጥሩ ጉጉት/ፍላጎት በውስጣቸው እንዲያድር ማድረግ ነው፡፡ በነዚህ በባህላዊ የድብልቅ መጠጦችና በተጠቃሚ ደንበኞቻችን መሐል የመጠጥ/የምርት አቅራቢዎቻችን ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የፈጠራው ባለቤቶችና ለድብልቅ መጠጦቹ ህይወትን የሚለግሱ ናቸው፡፡ ከስልጠና በኋላ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ተጨማሪ ሌሎች ስልጠናዎች የሚሰጡበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡ የሙያ ክለሳ ስልጠና፣ የኢንተርኔት አጠቃቀም ስርዓትና የሙያ ማጠናከሪያ ትምህርቶች በሚሰጡት ስልጠናዎች ውስጥ የሚካተቱ ይሆናል፡፡

- -