አዋሽ ወይን፣ አንጋፋው የወይን ጣዕም በኢትዮጵያ

Nov 7, 2019

አዋሽ ወይን ጠጅ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ከሰባ በላይ ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ ድርጅት ሲሆን፣ በወይን ማምረት ስረም የሀገሪቱ ዕድሜ ጠገብ ድርጅት ነው፡፡ በ117 ሄክታር መሬት ላይ በሚገኝ ከባህር ወለል 1200 ሜትር ከፍታ ባለው ተራራማ ስፍራ ላይ የሚገኘው የወይን አምራች በቅርቡ ደግሞ ተጨማሪ 180 ሄክታር ለማልማት ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡
ድርጅቱ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም ብሉ ናይል በተሰኘውና በታዋቂው የሪል ስቴት ባለሀብት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ እና በታዋቂው አቀንቃኝ እና የአፍሪካውያን መብት ተሟጋች ሰር ቦብ ጌልዶፍ በተመሰረተው ድርጅት ስር ከተጠቃለለ ጀምሮ የዕድገት ጉዞው እጅግ መልካመም ሆኗል፡፡ አቶ ሙሉጌታ እንደሚገልጹት፣ “የወይን ምርቱ ላይ የሚከናወነው ቀጣይነት ያለው ማሻሻያ፣ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወደ ድርጅቱ አሰራር መግባት እና ለድርጅቱ ሰራተኞች የሚሰጡ ስልጠናዎች የአዋሽ መልካም ዝና እና ብራድ በሀገሪቱ ውስጥ በጠንካራ ሁኔታ የሚገነቡ ናቸው፡፡”
የወይን እርሻው አቅም አስደናቂ ነው፡፡ የሚከናወኑት የዕድሳት ስራዎች በርካታ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የወይን መጥመቂያው ዕድሜ ጠገብ ቢሆንም ታድሶ በሚጠናቀቅበት ወቅት የወይን ጠጅ ምርቱ ጥራት በከፍታኛ ሁኔታ እንደሚሻሻል ይጠበቃል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ያለው አጠቃላይ አመታዊ የምርት መጠን ከ10 ሚሊዮን ሊትር እምብዛም የማያልፍ ሲሆን ይኸውም ሙሉ በሙሉ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ነው፡፡ ምንም እንኳን አዋሽ ወይን ከሀገር ውጪ ባሉ ደንበኞች ጥያቄ የቀረበለት ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ምርት ወደ ውጪ የመላክ ዕቅድ የለም፡፡ ይህም የሆነው በሀገር ውስጥ ያለውን የወይን ፍላጎት የሚያሟላ የምርት መጠን ገና ስላልመጣ ነው፡፡
የወይን ዕርሻ ቦታው የሚገኘው ከአዲስ አበባ በ115 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በአዋሽ መርቲ ጀጁ ቢሆንም ጎዟችን የደርሶ መልስ ነበርና ጉዟችንን የጀመርነው በማለዳ ነበር፡፡ በመስክ መኪና የሚደረገው ጉዞ 3 ሰዓት ከግማሽ ይወስዳል፣ ምንም እንኳን መንገዱ አስቸጋሪ ባይሆንም መንገዱን የተጓዝነው ግን በጥንቃቄ ነበር፡፡
መልክዓ ምድሩ እጅግ ውብ ነው፡ ጎጆ ቤቶች፣ ከወገባቸው በላይ ልብስ ያልለበሱ በቤታቸው ደጃፍ የሚጫወቱ ደስኛ ህጻናት፣ የማያልቅ የሚመስል በረሐ እና ግርማ ሞገስ የተላበሱ የዘንባባ ዛፎች እዲሁም ግመሎች መንገዳችንን በሙሉ አልተለዩንም፡፡
ሙሉውን ለማንበብ፡ http://www.wine-explorers.net/en/travelog/ethiopia-african-jewellery

- -