ኢትዮጰያዊው አዋሽ ወይን በ2 ሚሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ግንባታውን አጠናቀቀ፣ ዳንኪራ ምርትን በገበያ ላይ አውሏል

Nov 7, 2019

በኢትዮጰያ በወይን ማምረት ስራ ፈር ቀዳጅ የሆነው አዋሽ ወይን አ.ማ ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ያከናወነውን የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሲያጠናቅቅ የወይን ማምረት አቅሙንም አሳድጓል፡፡
በዚህ የማስፋፊያ ፕሮጀክት የተገነባው የማምረቻ ፋብሪካ ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ የተገጠመለት፣ የወይን ማጠቢያ እና መሙያዎችን ያሟላ እንዲሁም የቡሽ መግጠሚያዎችን እና የካፕሱል ማሸጊያዎችን እና ማድረቂያዎችን ያካተተ ነው፡፡ በዚህም ከሰው ዕጅ ንክኪ በጸዳ መልኩ ምርቶችን አምርቶ በማሸግ ከፍተኛ የሆነ የጥራት ደረጃን ለማሳካት እንደሚያስችል ተገልጧል፡፡ ይህ ማምረቻ የድርጅቱን የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ ሲሆን በወይን ማምረት ሂደት ውስጥ የሚኖረውን ብክነትም በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህም አሁን ያለውን ብቻ ሳይሆን ወደፊት ሊኖር የሚችለውን የገበያ ፍላጎትም ለማሳካት የሚያስችል እንደሆነ የድርጅቱ መግለጫ አመላክቷል፡፡
ዳንኪራ የተሰኘውን አዲሱን ምርት አስመልክቶ የድርጅቱ ብራንድ እና ኢኖቬሽን ኃላፊ ብርሀን መንግስቱ እንደሚናገሩት ድርጅቱ የደንበኞቹን ፍላጎት እና ምርጫ ለማሟላት አዳዲስ ምርቶችን እና ፈጠራዎችን በመጨመር ካለማቋረጥ ወደፊት የሚገሰግስ ድርጅት እንደሆነ አጽንዖት ሰጥተው ገልጠዋል፡፡
የድርጅቱ ኮሜርሺያ ዳይሬክተር ኔይል ኮምፎርድ ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገሩ፣ “ድርጅታችን በወይን ምርት ዕድገት ሂደቱ ውስጥ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ በመቻሉ ታላቅ ኩራ ይሰማዋል፣“ ብለው፣ “ወደፊትም ብራንዳችንን፣ ሰራተኞቻችንን እና ማህበረሰባቸንን በዘላቂነት በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ መዋዕለ ነዋያችንን ማፍሰሳችንን እንቀጥላለን፣“ ብለዋል፡፡
በ330 ሚ.ሊ ዕሽግ የቀረበው እና የአልኮል ይዘት ያለው ዳንኪራ በስትሮበሪ ማርጋሪታ እና በፒች ቮድካ ለገበያ ቀርቧል፡፡ ዳንኪራ ስሮበሪ ማርጋሪታ ከደረቀ የወይን ዘለላ፣ ከዕንጆሪ፣ አጋቬ፣ ቲኪላ እ ሊ,ሌሎች ተፈጥሪአዊ ፍሌቨሮች እንደሚዘጋጅ የብራንድ ማናጀሩ ገልጸዋል፡፡ ዳንኪራ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ በሚገኙ የመሸጫ ስፍራዎች በ330 ሚ.ሊ. ለሽያጭ የቀረብ ሲሆን የሚመከር የሽያጭ ዋጋውም ብር 25 ነው፡፡
ድርጅቱ የወይን ሰብል ምርቱን የሚያገኘው ቀድሞም ያስተዳድረው ከነበረው 517 ሄክታር መሬት ላይ ሲሆን በዚህ የዕርሻ መሩት ላላ ፔቲ ሳይራህ፣ ባርቤራ ናቢዮሎ እና ቼኒን ብላክ እንዲሁም ዶዶማ የተሰኙ የወይን ሰብሎችን ያመርታል፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ አንጋፋ የሆነው አዋሽ ወይን፣ በሀገሪቱ የወይን ምርት ገበያ ውስጥ 80 በመቶ የገበያ ድርሻ ያለው ሲሆን አዋሽ፣ ካሚላ፣ አክክሚት፣ ገበታ፣ አዋሽ ፕላስ እና ጉደር በተሰኙ ምርቶቹ ይታወቃል፡፡
እ.ኤ.አ በ1943 የተመሰረተው ድርጅቱ 11.5 ሚሊዮን ሊትር በሆነ አመታዊ የማምረት ዓቅም የኢትዮጵያ ትልቁ የወይን አምራች ነው፡፡
ካስቴል እና ቃና የተሰኙት እና ዓመታዊ የማምረት ዓቅማቸው 1.2 ሚሊዮን እና 500.000 ሊትር የሆኑት የወይን አምራቾች በሀገር ውስጥ ተፎካካሪዎቹ ናቸው፡፡
ምንጭ-https://www.foodbusinessafrica.com

- -