ሽርክና/አጋርነት ከህብረተሰቡ ጋር

ጃዝአምባ

የጃዝ አምባ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የወደፊቱን ትውልድ የሙዚቃ ልሂቃን እንኳን ደህና መጣችሁ ይላል፡፡ እዚህ በአዋሽ አክሲዮን ኩባንያበተከታታይ ግብዣዎች ላይ የኢትዮ-ጃዝ ድጋፋችንን በመለገስ ከጃዝ አምባ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ጋር ይበል የሚያሰኝ ሽርክና ይዘናል፡፡ በቁጥር 70 የሚሆኑ የሙዚቃ ተማሪዎችን ለመርዳት ከዝነኛና አንጋፋ የጃዝ አምባ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር ግንባር ፈጥረናል፡፡ እነዚህ የዛሬዎቹ የሙዚቃ ተማሪዎች የነገይቱ ኢትዮጵያ ድንቅ ሙዚቀኞችና የመስኩ ቁልፍ መዘውሮች ናቸው፡፡

የእርሻ ትምህርት ቤት


የሐረር ትምህርት ቤት፣ በሌላ ስሙ የእርሻ ትምህርት ቤት፣ የአዋሽ ወይን ፕሮጄክት መሆን የጀመረው ኩባንያው ገና በመንግስት ይዞታ ስር እያለበነበረበት ጊዜ ነው፡፡ በመቀጠልምየአሁኖቹ ባለሃብቶች፣ አቶ ሙሉጌታና (8 Miles LLP) ሃሳቡን ከልብ በመደገፍ ትምህርት ቤቱን በማገዝ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አድርገዋል፡፡

  • በየወቅቱ ለትምህርት ቤቱ የሚለገሰው የምግብ እርዳታ የተማሪዎች ቁጥር እንዲያድግ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
  • የመርቲ ትምህርት ቤት ከቅርብ ጊዜ በፊት የተጀመረ አዲሱ ፕሮጄክታችን ነው፡፡ ለትምህርት ቤቱ አዳዲስ መምህራንን ቀጥረናል፤ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን ገንብተናል፤ አዳዲስ ዴስኮችንና ጠረጴዛዎችን አቅርበናል፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች የትምህርት ቤት ዩኒፎርም አልብሰናል፡፡

የቦርድ አባሉ፣ ሚ/ር ሄሜን ሻህ በግላቸው የተማሪ ቦርሳዎችንና ልብሶችን ለሕፃናት ተማሪዎች ለግሰዋል፡፡

በግብርና ለተሰማራው ማህበረሰብ መድረስ

በግብርና ለተሰማራው ማህበረሰብ መድረስ

የግብርናውን ማህበረሰብ በመርዳት በኩል አዋሽ ወይን የራሱን ፈጠራ ተጠቅሞ ለውጥ አምጥቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የህብረተሰቡን የውሃ አቅርቦት ለማሻሻል ትልቅ ማከማቻ ገንብቶለግልጋሎት አብቅቷል፡፡ በቀጣይም የውሃ ተጠቃሚውን ህዝብ ለማሳደግ ቧንቧ የመዘርጋት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

የቆሼ አደጋ

የሰው ሃይል መምሪያችን ነበር በቆሼ አካባቢ በወገኖቻችን ላይየደረሰውን አደጋና መፈናቀልለመታደግ እርዳታ የማድረግን ሃሳብን ያመጣው፡፡ በዚህም መሰረት አዋሽ ወይን ኩባንያችን ለተጎዱ ወገኖቻችን የገንዘብና የአልባሳት ድጋፉን አድርጓል፡፡

መቄዶንያ

አዋሽ ወይን ኩባንያ ከመቄዶንያ ጋር ዝምድና የጀመረው፣ ከስድስት ዓመታት በፊት ከኩባንያው ሰራተኞች አንዱ አዛውንቶችን ስለመርዳት የወጣውን ማስታወቂያ በተመለከተ ጊዜ ነው፡፡ በጉዳዩ ልቡ በመነካቱ ወገኖቻችን ሊረዱ የሚችሉበትን መንገድ ለመፈለግ ወደኩባንያው ቀረበ፡፡ በአዋሽ ኩባንያ ውስጥ እምብዛም ጥቅም ላይ ያልዋሉ ቁሳቁሶች አልነበሩም፡፡ ስለዚህም ነው ይሄንን ለመቄዶን መለገስ የተቻለው፡፡

- -