እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከንግስት ሳባ ዘመነ-መንግስትና ከዚያም በላይ ለሆኑ ዘመናት የወይን መጠጥን የማምረት/የመጥመቅ አኩሪ ልምዱ አለን፡፡

ኩባንያው እ.አ.አ. በ1943 (1936 ዓ.ም) በሁለት የግሪክና የጣሊያን ቤተሰቦች ተመሰረተ፡፡ በ1973 እ.አ.አ. ወደ መንግስት ንብረትነት ከተሸጋገረ በኋላ አዋሽ ወይን በሚል ስም መጠራት ጀመረ፡፡

እ.ኤ.አ. በ1936 የተመሰረተው የአዋሽ ወይን ፋብሪካ በኢትዮጵያ ረጅም ዕድሜን የተጎናፀፈ የወይን መጠጥ ማምረቻ ማዕከል ነው፡፡ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በሃገሪቱ ውስጥ በጣም ተወዳጅ የሆኑ የወይን ምርቶችን የሚያቀርብና፣ የሃገሪቱን ባህላዊ ትስስር መሰረት አድርጎ በገበያ ውስጥ እየመራ የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡

በመስከረም 2005 (እ.ኤ.አ. 2013) (8 Miles LLP) በሰር ቦብ ጌልዶፍና በኢትዮጵያዊው ባለሃብት በአቶ ሙሉጌታ ተስፋ-ኪሮስ ወደግል ሃብትነት ከተሸጋገረ ጊዜ ጀምሮ አቅሙን ለማሻሻልና፣ የበለጠ ለማዘመን እጅግ ትልቅ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት እየተደረገለት ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዋሽ ወይን የኢትዮጵያን የወይን ምርት ገበያ እየመራ ይገኛል፡፡ እየተጠጡ ካሉት ከአስሩ የወይን ምርቶች ውስጥ ስምንቱ የአዋሸ ምርቶች ናቸው፡፡

- -