የአዋሽ የተግባር የስልጠና (ኢንተርንሺፕ) መርሐ-ግብር የላቀ ችሎታ ላላቸው የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ዕድሎችን ለመፍጠርና ጀማሪ ባለሙያዎች በገበያ፣ በሽያጭና በስራ አመራር ዘርፍ ትምህርት እንዲያገኙ በሚል የታለመ ነው፡፡ መርሐ-ግብሩ ከተጀመረ፣ ከ2013 አንስቶ ለ83 ተሳታፊዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ብዙዎቹ ተሳታፊዎች ለሃገር ውስጥ ቀጣሪዎች፣ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቡና ባንክ፣ ንብ ኢንሹራንስና የግብርና ትራንስፎርሜሽን በመሳሰሉት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ወይም የራሳቸውን የንግድ ስራ ለመጀመር ጥናታቸውን ቀጥለዋል፡፡

በገበያ ስራ የተግባር ልምምዴን የጀመርኩት በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ በ2015 ላይ ነው፡፡ በቆይታዬ ካስተዋልኳቸው ነገሮች ውስጥ አንደኛው የሰራተኞቹ ዝንባሌ ነው፡፡ በዚህ ኩባንያ ውስጥ ብልምምድ ላይ ባለሁ ጊዜ አመቺ የዕረፍት ሰዓቶችን እጠቀም ዘንድ ምርጫ ይሰጠኝ ነበር፡፡ ይሄም የቤተሰቦቼንና የራሴን ፍላጎት እንዳሟላ ዕድሉን ሰጥቶኛል፡፡ በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ መስራቴ የስራ ልምድ እንዳገኝ ብቻ ሳይሆን፣ ከሌሎች ሰራተኞች ጋርም ጥሩ ዝምድና እንድፈጥር አስችሎኛል፡፡ በይበልጥም በኢኮኖሚ ራሴን እንድደጉም አግዞኛል፡፡ በዚህ ዓይነት እኔና ቤተሰቦቼ ትልቅ የሚባል ጥቅም አግኝተንበታል፡፡ የተግባር ላይ ልምምዴን እንዳጠናቀቅሁ፣ ወዲያውኑ ተመርቄ በአሁኑ ሰዓት በኤሌክትሪካል ምህንድስና በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ግልጋሎት እየሰጠሁ እገኛለሁ፡፡

ስማቸው ፋሲካ

ከምረቃ በኋላ በገበያ የስራ መስክ በተግባር ተለማማጅነት በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ እንዳገለግል ዕድሉ ተሰጥቶኛል፡፡ ያገኘሁት ስልጠና በመስክ ስራ ላይ በምሆንበት ጊዜ እንዴት አድርጌ ሃላፊነቴን እንደምወጣ አስተምሮኛል፡፡ ይሄ ዓይነቱ መርሐ-ግብር አዳዲስ ተመራቂዎችን ለቀጣይ እርምጃቸው ይረዳቸዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ መስራቴ የራሴን የግንኙነት መረብ በሰፊው እንድዘረጋ አግዞኛል፡፡ ያጋጠሙኝ እንቅፋቶችና ፈተናዎች ትምህርት ሰጥተውኛል፡፡ በዚህም ፍፁም ደስተኛ ነኝ፡፡ ምክንይቱም በህይወት ባህር ውስጥ በፅናት እቀዝፍ ዘንድ ብርታት ስለሚሰጡኝ ነው፡፡ የስልጠና ቆይታዬ ትልቅ የስራ ጓዳዊነትና የአንድነት ስሜት እንዲኖረኝ አስችሎኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኤተል የማስታወቂያና ኮሙኒኬሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ውስጥ በፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነት ተቀጥሬ በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡ ለዚህ ሁሉ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡

እምነት እንዲህነው

የተግባር ላይ ልምምዴን በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ የጀመርኩት በ2015 ላይ በገበያ የስራ መደብ በረዳትነት ነው፡፡ ስልጠናው በተግበር ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ በመጀመሪያ በገበያ ትንተና የስራ ሂደት ልምድ እንዳገኝ ዕድሉ ተሰጥቶኛል፡፡ በተከታይም ከዴታ አሰባሰብ፣ የስራ አመራርና የሽያጭ ልምምዶችን ጨምሮ፣ እስከ የዴታ ኢንትሪና የትንተና ስራዎችን እንድለማመድ ሁኔታዎች ተመቻችተውልኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በገበያ ልማት ክፍል ውስጥ የስራ አመራር ዳይረክተሩ ረዳት በመሆን አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡

ማህሌት

- -