ሃርቬ ዱራንቶን

ማናጂንግ ዳይረክተር

ተጨማሪ ያንብቡ

አዋሽ ወይንን ከመቀላቀሉ በፊት፣ ሚ/ር ሃርቬ ዱራንቶን ከተዋጣለት የስራ ልምድ ጋር በዋና ስራ እስኪያጅነት በፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና አረብኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሃገሮች ውስጥ አገልግሏል፡፡ በነዚህ ቦታዎች የቡድን ስራ አመራር፣ ተሰጥዖ፣ የአንተርፕረነርና የስራ አመራር ክህሎቶችን አበልፅጓል፡፡ ሚ/ር ሃርቬ ከተለያዩ ድርጅቶች የሚከተሉትን የሥራ ልምዶች አካብቷል፡፡ቤልጂየም ውስጥ ባለው ግሩፕ ዩኒብራ በተባለ መስሪያ ቤት ውስጥ በጠመቃ ክፍል፤ ኢኳቶሪያል አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ሞሮኮ፣ ጊኒና ግብፅ ውስጥ ባሉ የኔስል ኩባንያዎች በዋና ስራ አስኪያጅነት፡፡ሃርቬ በሥራ አመራር ከኢኮል ሱፒሪየር ደ ኮሜርስ ቸልርሞንት የማስተሬት ድግሪውን አግኝቷል፡፡

ስንሻሽ ተሰማ

ፋይናንስ ዳይሬክተር

ተጨማሪ ያንብቡ

ስንሻሽ ተሰማ ሁለት የሁለተኝ ዲግሪ ያላት ሲሆን የመጀመሪያው በባንኪንግና ፋይናንስ ከሶቦን ዩኒቨርሲቲ፣ ፈረንሳይ ሁለተኛውን ደግሞ በፋይናንስ ማርኬት ከፖሊቲየርስ ዩኒቨርሲቲ፣ ፈረንሳይ ያላት ሲሆን በተጨማሪም በማኔጅመንትም ዲግሪ ይዛለች፡፡ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን ከመቀላቀሏ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ለአፋር አላን ፖታሽ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል የአክሲዮን ኩባንያ በፋይናንስ ተቆጣጣሪነት ሰርታለች፡፡

ግርማ በለው

የኮርፖሬት ጉዳዮች ዳይሬክተር

ተጨማሪ ያንብቡ

ግርማ በኢንፎርሜሽን ሲስተም ሁለተኛ ድግሪ፣ በንግድ ስራ አመራር ደሞ የመጀመሪያ ድግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በፕሮጀክት ስራ አመራር የምስክር ወረቀት ተቀብሏል፡፡ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን ከመቀላቀሉ በፊት ግርማ ለአሜሪካው ፕላንድ ፓሬንትሁድ ፌዴሬሽን በቡድን መሪነት ለአንድ ዓመት አገልግሏል፡፡ በተጨማሪም ግርማ በለው እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በኦፐሬሽን ዳይረክተርነት ለአንድ ዓመት ኢትዮ ጆብስን አገልግሏል፡፡

ሄኖክ በላይ

የልደታ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ

ተጨማሪ ያንብቡ

ሄኖክ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪውን በአፕላይድ ኬሚስትሪ፣ አዲስ አበባ በሚገኘው ግሪን ዊች ኮሌጅ ደሞ በዓለም-አቀፍ የንግድ ጥናት ሁለተኛ ድግሪውን አግኝቷል፡፡ በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ከመቀጠሩ በፊት፣ አሰላ በሚገኘው የብቅል ፋብሪካ ውስጥ በኬሚስትነት ለአንድ ዓመት አገልግሏል፡፡ በተጨማሪም አዲስ አበባ በሚገኘው አይ ዞን እየተባለ በሚጠራው ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ውስጥ ለአንድ ዓመት በገበያ ልማት ሰራተኝነት አገልግሏል፡፡

እዮብ አሳምነው

የመካኒሳ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ

ተጨማሪ ያንብቡ

እዮብ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ኮሚስትሪ የመጀመሪያ ድግሪ፣ ሁለተኛ ድግሪውን ደሞ በአካባቢ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወስዷል፡፡ እዮብ ሥራ የጀመረው በአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያበኬሚስትነት ሲሆን ከዘጠኝ ዓመታት ግልጋሎት በኋላ የመካኒሳ ፍብሪካ ስራ አስኪያጃችን ሆኗል፡፡

ዳኜ በላይ

የግብርና አማካሪ

ተጨማሪ ያንብቡ

ዳኜ በእፅዋት ሳይንስ የትምህርት መስክ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ድግሪውን አግኝቷል፡፡ ሥራ የጀመረው በኢትዮጵያ የግብርና ኢንስቲቲዩት ሲሆን፣ በዚሁ መስሪያ ቤት በከፍተኛ የቴክኒክ ረዳትነት ሰፋ ያለ የስራ ልምድ አካብቷል፡፡ ዳኜ ለግብርናው ኢንዱስትሪ የዘዎትር የጋለ ፍቅር ስላለው፣ በዚሁ መስክ ሥራውን ቀጥሏል፡፡ እንዲሁም በግብርና የስራ አስኪያጅ መደብ የአሰላን ሞዴል የግብርና ድርጅት አገልግሏል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ከአዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያ ቤተሰብ ጋራ ተቀላቀለ፡፡ በዚህ ዓይነት ዳኜ ከእኛ ጋር ለስድስት ዓመታት ሰርቷል፡፡

ፀሐዬ ዘረሰናይ

የጥራት ቁጥጥር ስራ አስኪያጅ

ተጨማሪ ያንብቡ

ፀሐዬ በያዘው የስራ መስክ የካበተ ልምድ ይዞ ነው የመጣው፡፡ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን ከመቀላቀሉ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ የመድሃኒት አምራች አክሲዮን ኩባንያ (ኢፋርም) ውስጥ በከፍተኛ የኢንስትሩሜንታል ተንታኝነት፣ በከፍተኛ የኬሚስት ተመራማሪነትና የጥራት ቁጥጥር ሃላፊነት አገልግሏል፡፡ የትምህርት የምስክር ወረቀቶቹ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመድሀኒት ትንተናና የጥራት ማረጋገጫ የመጀመሪያ ድግሪና በፋርማሲ የትምህርት መስክ ደሞ ዲፕሎማን ያካትታሉ፡፡

ሐይማኖት ወ/ፃዲቅ   

ኢ.ኤች.ኤስ. አማካሪ

ተጨማሪ ያንብቡ

ሐይማኖት ትምህርቷን የተከታተለችው በሩሲያ ሲሆን፣ ከቮልጎ ግራድ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ስነ-ህይወት (ባይዎሎጂ)፣ ኬሚስትሪና ግብርና አጥንታለች፡፡ ሁለተኛ ድግሪዋን ከያዘች በኋላ በጥራት አስተዳደር የትምህርት መስክ አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው ሮችቪል ኦን ላይን (የመፃፃፍ) ዩኒቨርሲቲ ፒ.ኤች. ድግሪዋን በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ ሐይማኖት በኢትዮጵያ የሕዝብ ጤና ኢኒስቲቲዩት ውስጥ በፓስተርነት ነው ስራዋን የጀመረችው፡፡ በመቀጠልም የራሷን ንግድ ለመጀመር በመወሰን ጎልደን ብሪጅ የምክር አገልግሎት የሚል ድርጅት ከፈተች፡፡ በ1975 አ.ኤ.አ. አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን በመቀላቀል እስካሁን ከእኛ ጋር እየሰራች ትገኛለች፡፡

ሪቻርድ ኦተር

ወይን ማስተርና የእርሻ ማኔጀር

ተጨማሪ ያንብቡ

ሪቻርድ ኦተር አዋሽን የተቀላቀለው በቪቴ ካልቸር ማስተር ሲሆን  በቪቴ ካልቸር አኖሎጅ፣ በቢዝነስ እና ትሬድ የስራ መደቦች በአማካሪነት እንዲሁም በቴክኒክ ማናጀር፤ በአስተማሪነት፤ በወይን ሜከር እና በቬንያርድ ከርየሽን በተለያዩ ድርጅቶች የ27 አመታት የስራ ልምድ ያካበተ ነው፡፡

ማክሲም ዴማሬክስ

ወይን ማስተርና ምክትል የእርሻ ማኔጀር

ተጨማሪ ያንብቡ

ማክሲም አዋሽን የተቀላቀለው የወይን እርሻን እና የሴላር ቡድኖችን ለማገስ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከወይን ማስሩና ከእርሻ ሀላፊው ጋር በቅርበት የሚሰራ ነው፡፡ በትምህርት የግብርና ምሩቅ ሲሆን በግብርና ማህበራትና ጥናት ላይ ከፍተኛ ልምድ ያለው ነው፡፡ ማክሲም እ.ኤ.አ ከ 2015 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በወይን ዝርያና በወይን ጠመቃ ላይ መስራት የጀመረ ሲሆን ለ2 አመታት በፈረንሳይ የወይን ምርትና መጠጥ ኢኒስሲትዩት አገልግሏል፡፡

- -