ተልእኮ

ኢትዮጵያውያን ለወይን ያላቸውን ፍቅር እና አድናቆት ብሎም የአለም ህዝብ ለኢትዮጵያ ወይን ያለውን አድናቆት ከፍ የሚያደርጉ ወይኖችን ማቅረብ፡፡

ራዕይ

ራዕያችን  እ.ኤ.አ 2030 ጥራት ያላቸው በወይን እና በወይን ላይ በተመሰረቱ ምርቶች ታዋቂ የሆነ የወይን አምራች መሆን ነው፡፡

እሴቶቻችን

ህብረት

የእግር ኳስ ቡድኖች ካለ ትብብር እና አንድነት ምርጥ አቋም ማሳየት እንደማይችሉት ሁሉ እኛም ማንም በተናጠል የቆመ አካል ከህብረታችን እንደማይበልጥ እናምናለን፡፡

ይህንን እሴት በተግባር የምንኖረውም
የጋራ ግቦቻችን ከግል ወይም ከስራ ክፍላችን የተናጠል ግቦች የበለጠ ጠቃሚ እንደሆኑ በመረዳ
ሌሎች ድክመት በሚያሳዩባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ድጋፍ በመስጠት
ጠቃሚ እና ገንቢ ለሆነ እንዲሁም ወቅቱን ለጠበቀ አስተያየት ክፍት በመሆን እና ይህን መሰል አስተያየቶችን በመስጠት
ሌሎችን ከመወንጀል እና ስለ ሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና የአስሳሰብ ሁኔታ የችኮላ ውሳኔ ከመስጠት መቆጠብ

ጥልቅ ፍቅር

ስኬት የሚመነጨው እያንዳንዳችን ለምንሰራው ስራ ካለን ፍቅር ነው፡፡

ይህንን እሴት በተግባር የምንኖረውም
ስራችንን ስንሰራ ለራሳችን እንደምንሰራው በመስራት
ግባችንን በፍጹማዊነት ለመስራት በማለም
ለሚፈጠሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉ መፍትሄዎችን በትጋት በመፈለግ
የምናልመውን ለውጥ ለማምጣት ሁልጊዜም በፍላጎት፣ ወቅቱን በጠበቀ ሁኔታ እና በእምነት በመስራት

ዕምነት

ስኬት የሚመነጨው እያንዳንዳችን ለምንሰራው ስራ ካለን ፍቅር ነው፡፡

ይህንን እሴት በተግባር የምንኖረውም
ስራችንን ስንሰራ ለራሳችን እንደምንሰራው በመስራት
ግባችንን በፍጹማዊነት ለመስራት በማለም
ለሚፈጠሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉ መፍትሄዎችን በትጋት በመፈለግ
የምናልመውን ለውጥ ለማምጣት ሁልጊዜም በፍላጎት፣ ወቅቱን በጠበቀ ሁኔታ እና በእምነት በመስራት

 

ስራ ፈጣሪነት

መስራት ምንም ካለመንቀሳቀስ የተሻለ በመሆኑ የተላንት የስኬት መንገዶች በቋሚነት መፈተሽ እና በፍጥነት ከሚለዋወጠው ዓለም ጋር መጣጣም አለባቸው፡፡ ምርጥ ከሆኑ አዳዲስ ውጤቶች ፈጠራ ከታከለባቸው ሀሳቦች እና ድፍረት ከታከለበት አሰራር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

ይህንን እሴት በተግባር የምንኖረውም
ስህተት ለመስራት ባለን ፍርሀት ላይ ሳይሆን ከስህተቱ በመማር ላይ በማተኮር
ለአዳዲስ ሀሳቦች፣ ለአዳዲስ አሰራሮች ወዘተ ክፍት በመሆን እና ሀሳቦችን ከጅምሩ ሳንሱር ከማድረግ በመቆጠብ እንዲሁም ለፈጠራ በራችንን ክፍት በማድረግ እና አዳዲስ ሀሳቦች እንዲፈጠሩ እና እንዲያድጉ በማበረታታት

- -