አዋሽ ወይን የአፍሪካ ፕራይቬት ኢኪዩቲ የአመቱ ተሸላሚ ሆነ

አዋሽ ወይን አ.ማ በእንግሊዝ ሀገር በተካሄደው የአፍሪካ ፕራይቬት ኢኪዩቲ(Private Equity Africa) ውድድር የአመቱ ተሸላሚ ድርጅት በመሆን የዋንጫ ሽልማት አግኝቷል፡፡ ባጠቃላይ ውድድሩ ላይ ከቀረቡት 15 የሚሆኑ አፍሪካ ውስጥ ያሉ የአፍሪካ ፕራይቬት ኢኪዩቲ ጅርጅቶች ውስት ተወዳድሮ ባለፉት ጥቂት አመታት የላቀ የስራ አፈፃፀም በማሳየት ነው አዋሽ ወይን አ.ማ ለሽልማት የበቃው፡፡ እንኳን ደስ አለን፣...

የወኪሎች ኮንፍረንስ

ወኪሎቻችን ዋንኛ የቢዝነስ አጋሮቻችን በመሆናቸውና ይህንንም ላማጠናከር በየስድስት ወሩ የምናዘጋጀው ኮንፍረንስ አካል የሆነው የወኪሎች ኮንፍረንስ ከመጋቢት 8-11 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ የኮንፍረንሱ አላማም ከወኪሎቻችን ጋር የጋራ መድረክ እንዲኖረን እና የስትራቴጂክ አጋርነታችንን ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡ በኮንፍረንሱም ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ 60 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ አዳዲስ መረጃዎች...

የአዋሽ ወይን ጠጅ ሰራተኞች በታላቁ ሩጫ ተሳተፉ

ህዳር 17.2010 ዓ.ም በተካሄደው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 150 የአዋሽ ወይን አ.ማ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ከጥቂት አመታት ወዲህ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ ደማቅ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት የድርጅቱ ሰራተኞች እንዲህ ያለው የስፖርት ውድድርና ተሳትፎ የሰራተኞቹን የአካልና የአእምሮ ጤና ከመጠበቅ ባሻገር በስራ ቦታዎች ላይ መልካም ግንኙነት እና የስራ ተነሳሽነት በመፈጠር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን...

ሠራተኞች በዳሽን እና ሐበሻ ቢራ የስራ ጉብኝት አደረጉ

የአዋሽ ወይን ጠጅ አ.ማ ሰራተኞች ጥቅምት 28 እና 30 2010 ዓ.ም ደብረብርሀን በሚገኙት የዳሽን ቢራ እና የሐበሻ ቢራ አ.ማ ፋብሪካዎች የመስኩ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የሁለቱም ኩባንያ ባለሙያዎች ለጎብኚዎቹ ስለ ቢራ አጠማመቅ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም በቢራ ጠመቃ ወቅት ለጥራትና ደህንነት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡ አክለው አብራርተዋል፡፡ በጎብኚዎችም የቀረቡላቸውን በርካ ጥያቄዎች ተገቢውን...

የ 2010 ዓ.ም አመታዊ የሰራተኞች ክብረበዓል

“በአዲስ አመት ታላቅ ውጤት” በሚል መሪ ቃል የአዋሽ ወይን አ.ማ ሰራተኞች መስከረም 28፣ 2010 ዓ.ም በያያ ቪሌጅ አመታዊ ክብረበአላቸውን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች አና አዝናኝ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ አክብረው ውለዋል፡፡ ሰራተኞቹ የተሰባሰቡትም ከልደታ መካኒሳና መርቲ ጀጁ ሲሆን ብዝሃነትን ያሰተናገደም ነበር፡፡ የተለያዩ የስፖርታዊ ክንውኞች የክብረበዐሉ አንድ አካል የነበረ ሲሆን ብዙ ሰራተኞችም በመሣተፍ አስደሳጭ...

የሰራተኞች የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ

አዋሽ ወይን ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር ለ38 ሰራተኞች የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና ተሰጠ፡፡ አዋሽ ወይን ጥሩ የመግባቦት ችሎታ የካምፓኒውን ግብ ለማሳካት አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል፡፡ የስልጠናው አላማም ለተሳታፊዎች ጥሩ የመግባቦት ችሎታን ለማካበት ያለመ ነው፡፡ ስልጠናውም በሶስት የተከፈለ የተለያዩ ደረጃዎች የተከከፋፈለ ነበር፡፡ የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሰው ሃብት አስተዳደ ዳይዴክተር ስለ መሰል...

የአዋሽ ወይን የወኪሎች ኮንፍረን

የአዋሽ ወይን ወኪሎች ኮንፍረንስ ከነሀሴ 19-21 2009 ዓ.ም በውቢቷ ሀዋሳ ተካሂዷል፡፡ ይህም ከወኪሎቻችን ጋር የጋራ መድረክ እንዲኖረን እና የስትራቴጂክ አጋርነታችንን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ ፈጥሮልናል፡፡ ...

የአለም አቀፍ ተማሪዎች ጉብኝት

ጀርመን ሀገር ከሚገኘው ጌስቼም ዩንቨርሲቲ የተወጣጡ በርካታ ተማሪዎች በአዋሽ ወይን  የልምድ ልውውጥና የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ አላማውም ስለ ሀገራችን ወይን እና የምርት ሂደት ስራ ልምድ ለመቅሰም ነው፡፡ በአስደሳቹ ጉብኝት ፋበሪካውን እና የምርት ሂደቱን ጎብኝተዋል፡፡ከጉብኝቱም በኋላ ተማሪዎቹ ስለ ፋብሪካው የስራ ባህል እና የምርት ሂደት አጠቃላይ ግንዛቤ አግኝተዋል፡፡ ለጥናታቸውም ውጤትን...