በ2013 በለንደን የሚገኘው 8 ማይልስና (8 Miles LLP) የሃገር ቤቱ ባለሃብት ሙሉጌታ ተስፋ-ኪሮስ ግንባር ፈጥረው የወይን ማምረቻ ኩባንያውን በገዙ ጊዜ አዋሽ ወይን ወደግል ንብረትነት ተሸጋገረ፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ኩባንያው ለማሽኖችና ለገበያ፣ እንዲሁም ለወጪና ብክነት ቅነሳ መርሐ-ግብሮች ከፍ ያለ መዋዕለ ንዋይ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ‹‹ኩባንያው ወደግል ንብረትነት ያደረገውን የሽግግር ሂደት ካጠናቀቀ በኋላ፣ ከመንግስት ኩባንያዎች የሚጠበቀውን ዋና ዋና የአቅም ውስንነቶች አንፀባርቋል፤›› በማለት ያስታውሳሉ የኩባንያው አጋር፣ ዳውግ አግበል፡፡ ‹‹እነዚህን ድክመቶች ለመፍታት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ለመመደብ፣ ያላሰለሰ ጥረት ለማድረግና የባለሙያዎችን ተስጥዖ ለመጠቀም የተወሰደው ቆራጥ እርምጃ፣ ዛሬ ኩባንያው የደረሰበትን የእድገት ደረጃ እንዲቆናጠጥ ከማስቻሉም በላይ ትርፋማነቱንም ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ እንዲያሻሽል እድርጎታል፡፡ ኩባንያውን ወደሚፈለገው የለውጥ እርከን ለማስገባት በሁሉም የሰራ እርከኖች ሰራተኛውን በማበረታቻና በስልጠና ማስታጠቅ ቅድሚያ የተሰጠው ተግባር ነው፡፡››

- -