በ517 ሄክታር ለም መሬት ላይ የተንጣለለው የላይኛው አዋሽ ሸለቆ ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በ180 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በ100 ሄክታር የእርሻ ሜዳ ላይ እየለማ የሚገኘው የወይን ተክል ፔቲ ሲራህ፣ ባርቤራ፣ ነቢሎ፣ ቼኒን ብላንክና የኛው ሃገር በቀል ዶዶማ የተባሉ ዘሮችን አካቷል፡፡ የእርሻ መሬቱ ለወይን ተክሎች በሚስማማ አፈርና አየር ጠባይ የታደለ ነው፡፡ አዋሽ ወይን አክሲዮን ኩባንያን የተለየ የሚያደርገው በወይን እርሻው ላይ በዓመት ሁለት ጊዜ የወይን ምርት መሰብሰብ መቻሉ ነው፡፡

አስደሳች በሆነ ቦታ ላይ የመርቲ ጀጁ የወይን እርሻችን ይገኛል፡፡ የወይን ዘለላዎች ከዚህ ቦታ ተመርተው/ተሰብስበው ወደ ሁለቱ የወይን ጠጅ ማምረቻ ፋብሪካዎቻችን፣ ልደታና መካኒሳ፣ ይጓጓዛሉ፡፡ ስድስቱን የተለዩና ግሩም የሆኑ የወይን ምርቶቻችንን በነዚህ ፋብሪካዎች ውስጥ በአሁኑ ሰዓት እያመረትን እንገኛለን፡፡

- -