ልደታ

ልደታ የአዋሽ ኩባንያ አስተዳደርና የወይን መጠጥ ማምረቻ ዕምብርት ነው፡፡ የልደታ ወይን ፋብሪካ አክሱሚት ቀዩንና ካሚላ ነጩን ጨምሮ 70 ከመቶ የሚሆነውን የወይን ጠጅ ያመርታል፡፡ ልደታ በግሪካውያን ቤተሰቦች የተመሰረተ በኢትዮጵያ ሁለተኛው የወይን አምራች ኩባንያ ነው፡፡ ግሪካውያኑ በዱከምና ጉደር እርሻቸው ላይየራሳቸውን ትኩስ የወይን ሰብል ይሰበስቡ ነበር፡፡ የመጀመሪያውን የወይን ጠጅ ምርት በሴት ልጃቸው ስም ሳሪስ ሲሉ ሰየሙት፡፡ በኋላም የጉደር ወይንን ማምረት ጀመሩ፡፡

መካኒሳ

የመካኒሳው ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ዳርቻ ላይ በስዕሎች ባጌጠችው የኪዳነ-ምህረት ቤተ-ክርስቲያን አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ቅርንጫፉ ከሌሎች ሁለት የወይን ማምረቻዎቻችን ጋር ሲነፃፀረር በዕድሜ አንጋፋና 30 ከመቶውን አጠቃላይ የኩባንያውን የወይን መጠጥ ማምረት የሚችል ነው፡፡

 

መካኒሳ በጣሊያናውያን የንግድ ሰዎች በኢትዮጵያ የተመሰረተ የወይን ማምረቻ ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው በአክሲዮን ባለድርሻዎች በንብረትነት የተያዘ ነው፡፡ በድሮ ጊዜ ግራፓ አረቄ፣ መካኒሳ ነጭ የወይን ጠጅና ደረቅ ነጭወይን ይመረትበት ነበር፡፡ መካኒሳ የአዋሽን ከፍተኛ ምርት ያመርታል፡፡ ለመጪዎቹ ስድስት ወራትም ይዞታውን ያስፋፋል፡፡ ከዚህ የማስፋፋት ስራ በኋላም የአዋሽና ጉደር የወይን ምርቶች በከፍተኛ መጠን ይጨምራሉ፡፡

- -